ይህ የመረጃ ቋት /the database/ በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭው ዓለም ቤተ ክርስቲያን ነክ የሆኑ መረጃዎችን ለምእመናንና ቤተ ክርስቲያኗን ለሚፈልጓት ሁሉ ማድረስን ዐቢይ ዓላማው አድርጎ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ማኅበረ ቅዱሳን አሲቲ(ICT) ዋና ክፍል ተዘጋጅቷል። ይህ ዝግጅት ቤተክርስቲያናችንን አስመልክቶ በዓይነቱም ይሁን በይዘቱ የመጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን በሒደት እየዳበረ የሚሄድና የሁሉንም የቤተ ክርስቲያን አካላት ሱታፌ የሚጠይቅ ነው። በመሆኑም የመረጃ ቋቱ ተጠቃሚዎች ይጠቅማል የምትሏቸውን መረጃዎችን በመላክ ሱታፌ እንድታደርጉ የመረጃ ቋቱ ዝግጅት ክፍል በዚሁ አጋጣሚ ጥሪውን ያስተላልፋል። መረጃዎችን በዚህ ገጽ፣ አስተያየትዎን ደግሞ በዚህ ገጽ፣ እንዲልኩልን በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
ተጨማሪ ያንብቡ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ማኅበረ ቅዱሳን አሲቲ(ICT) ዋና ክፍል
ሀገር |
|
|
ግዛት |
|
|
|